ሃይማኖቶች
ለምድራችን መልካም ገጽታ ግንባታና
ለዜጎች በሰላም ወጥቶ መግባት አስተዋጽኦ
አላቸው። ሁሉም ሃይማኖቶች የራሳቸው
አስተምህሮ አላቸው፡፡ ሁሉም ሃይማኖቶች “ትክክል ነን” ብለው ያምናሉ። ተከታዮቻቸውም ደም እስከማፍሰስ ድረስ ይሰውላቸዋል።
ምድራችን
የተለያዩ አመለካከቶችና የሚጠላሉ
ሃይማኖቶችን ተሸክማ ወደ ፍፃሜ እየገሰገሰች ነው። በሚጠላሉት ሃይማኖቶች ውስጥ የሚግባቡ ዶክትሪኖች አሉ፡፡
በሃይማኖቶች ልዩነት ውስጥ የጋራ ስምምነቶች አሉ፡፡
ሃይማኖቶች
ሰውን በተመለከተ የጋራ ከለላ ይሰጣሉ።
ማንም ሰው በራሱ እንዲደረግበት የማይፈልገውን
በሌሎች ላይ ማድረግ እንደሌለበት ያስጠነቅቃሉ። እንዲደረግለት የሚፈልገውን ደግሞ ቀድሞ ለሌሎች እንዲያደርግ ይመክራሉ።
ዛሬ
ላይ ሃይማኖቶችን ስንመዝን ከሚያምኑበት በተቃራኒ ሲጓዙ፤ ሰውን ሲያደነዝዙ፤ እርስበእርሳቸው ሲነቃቀፉና የሞት ሕግን ሲያውጁ አየን። ሃይማኖቶች ከተፃፈው ዶክትሪን በተቃራኒ የሚጓዙ አማኞች የበዙበት የወንበዴዋች ዋሻ እየሆኑ ነውና አስተውለን እንጓዝ፤ እየጠፋ ያለውን ትውልድ እንታደግ።
ሰው ሆነን ሰውን አንጉዳ!!
No comments:
Post a Comment