- በጥቂቱ ታመን እግዚአብሔር በብዙ ያከብርሃል፡፡
- በጲጥፋራ ቤት ካልረከስክ እግዚአብሔር በግብፅ ይሾምሀል፡፡
- መንገድህን ያለነውር ብትጓዝ ጽድቅ ይጠብቅሀል፡፡
- በምትችለው ከታመንክ አምላክህ የማትችለውን ያስችልሀል፡፡
- የልብህን መሻት ለእግዚአብሔር ከመንገርህ በፊት አስቀድሞ በቃሉ የነገረህን አስብ፡፡
- እግዚአብሔር እንዲያደርግልህ ከመለመንህ በፊት ቀድሞ ስላደረገልህ ሁሉ አመስግነው፡፡
- ለእግዚአብሔር ባስያዝከው ጉዳይ እንደገና አትጨነቅ፡፡
- ለወንድምህ መዳን ድከም እንጂ ለመጥፋቱ ምክንያት አትሁን፡፡
- ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፤ ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን፡፡
- ለደካሞች ትጋ፤ የወደቁትን አንሳ፤ ያዘኑትን አጽናና፤ ብድራትህን ፀሐይ ወደማደሪያዋ ሳትመለስ ታየዋለህ፡፡
- ለዐይን አምሮትህና ለሥጋ መሻትህ ብለህ ለቤዛ ቀን የታተምክበትን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝን፡፡
- እንደ ዘመኑ ሳይሆን እንደ ቃሉ ኑር፡፡
- እግዚአብሔርን በመፍራት ተመላለስ ከመከራ ይጋርድሃል፡፡
- መከራ ያልነካው ሰውና እሳት ያልነካው ሸክላ አንድ ናቸው፤ ቶሎ ይፈርሳሉና፡፡ ስለዚህ መከራን በደስታ ተቀበል፡፡ ጠላት ከሌለህ ትግል፤ ያለ ትግል ደግሞ የድል አክሊል የለህምና የጸናውን እያሰብክ፤ በፊትህ ስላለው ደስታ እየታገስክ ጸንተህ ታገል፡፡
- መልካም መስሎ የሚታይህ መንገድ ወደ ሞት እንዳያደርስህ ጉዞህ በማስተዋል የተጋረደ፤ በጥንቃቄ የተጠበቀ ይሁን፡፡
- ያለ መልካም ምክርና ያለ እምነት ሰልፍ አታድርግ ትሸነፋለህና፡፡
- እንዳትጎዳ ክፉ ቀን እስኪያልፍ በአባትህ እቅፍ ተሸሸግ፡፡
ይቀጥላል…
No comments:
Post a Comment