የዘመናት
ጭንቀት ዋይታ- የስቃዩ ጦር ተደመሰሰ
የጠላት
ክፉ ምኞት- እኩይ ምሽጉ ተገረሰሰ
ለአእምሮ
ስቃይ የሆነው- አስፈሪ ገደል ተናደ
ቃጠሎ
ጨርሶ ጠፋ- ሰደድ እሳቱ በረደ
እንክትክት
አለ ወደቀ- የእስራቱ ካቴና
የባርነት
ጉም ገፈፈ- ተሰባበረ ጭቆና
ትካዜ
መቆም አቃተው- ሀዘን እራቀ ነጎደ
ደስታ
ተናኘ ፋነነ- ፍቅር ከሰማይ ወረደ
አዳም
ጨለማን ተለየ- ከብርሃን ጋር ተዛምዶ
ፀሐየ
ጽድቅ ክርስቶስ- ከዳግማዊት ሰማይ ተወልዶ
ላይገዛ
ዓለም እንደገና- ላይተክዝ በከንቱ
በተሰቀለው
ክርስቶስ- ሞቱ ጠፋለት በሞቱ
ከዐጸደ-ወይን የግጥም መድብል የተወሰደ
No comments:
Post a Comment