-
ሕይወት
ብርቱ ሰልፍ ናትና ትጥቅ ያስፈልጋታል፡፡ ትጥቁም የመንፈስ ሰይፍ ነው፡፡ ስለዚህ ክፉን ቀን ለመቋቋም እንድትችል የእግዚአብሔርን
እቃ ጦር አንሳ፡፡
-
መልካም
እድል ወደ አንተ በቀረበ ጊዜ ፈጥነህ ያዘው ካመለጠህ ግን ልታገኘው አትችልም፡፡
-
ቤትህን
እንደ እግዚአብሔር ቃል ከመራኸው መላእክት አብረውህ እንዲኖሩ ልትጠራቸው ትችላለህ፡፡
-
ገንዘብ
ሊገዛው የማይችለውን ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስ ባዕለጠግነት ገንዘብ አድርግ፡፡
-
መልካምነት
በክርስቶስ ዳግም የተፈጠርክበት ዓላማ ነውና ሳትሞክረው አትዋል፡፡
-
መልካም
ሥራህ እግዚአብሔርን ለማክበር እንጂ ለትምክህት አይሁን፡፡
-
የሚጠብቅህ
አይተኛምና በጠላትህ መንቃት አትስጋ፡፡
-
የማትበላውን
አታጥምድ፤ የማታወርደውን አትስቀል፤ የማትፈታውን አትሰር፡፡
-
ስታስብ
ፈቃዱን፤ ስትጀምር እርዳታውን ጠይቅ፤ ስትጨርስ እጅህን ለምስጋና
አንሳ፡፡
-
የምታመልከውን
እወቅ፤ ያወከውን እመን፤ ላመንከው ታመን፤ ላመንከው ኑር፤ ለክርስቶስ በክርስቶስ ኑረህ ሙት፡፡
ይቀጥላል…
ቤተ ፍቅር፤ ጥሩ ጽሁፍ ነው። አንዳንዶቹ ጥሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያላቸው ስለሆኑ ተጠቅሜባቸዋለሁ። በዚሁ ቀጥል!!!
ReplyDeleteከዚሁ ጋር አያይዤ የምገልጽልህ የትዊተር በራሪዋ ወፍ /ፎሎው ሚ/ የሚለውን ተከትዬ ያንተን የትዊተር ገጽ ለማየት ብሄድ ገጹ ያንተ አይደለም። ኮዱን ያመጣህበት /goodinblogging.blogspot.in/ የሚለው የ«ሳይኪራንሳማ» የትዊተር ገጽ ነው። በራሪዋ ወፍ /tweet this/ /follow me/ የምትል ስለሆነ ይህንኑ አስተካክል። አንተ የተጠቀምብክበትን ኮድ ውስጥ ከታች ያለውን ክፍል ውስጥ /saikiransama/ የሚል የብሎገሩ ስም ሁለት ቦታ ስላለ በራስህ የትዊተር ስም ቀይረው። ያኔ ይስተካከላል። አለበለዚያ በራሪዋን ወፍ አንተ መጠቀም የፈለከው ለጌጥ ይመስላል። ግን የሰውን የትዊር ገጽ ነው የምትጠቀመው። ምናልባት ህንዳዊው ሳይኪራንሳማ አንተ ትሆን እንዴ? መልካም ጊዜ ይሁንልህ።
http://www.twitter.com/saikiransama"///////////////
/saikiransama.json?callback=twitterCallback2&count=1
ለገንቢ ሃሳበዎ እግዚአብሔር ይስጥልን!!!
Delete