Thursday, August 16, 2012

ሰበር ዜና-ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አረፉ


በብዙ ሕመም፣ባልተረዱአቸው ሰዎችና በክፉዎች ጉባኤ ሲቆስሉ የኖሩት ታላቅ አባት በባልቻ ሆስፒታል እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው ዛሬ ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በተወለዱ በ76 ዓመታቸው አረፉ፡፡ በሰቡ አማርኛዎቻቸው፣ባማረ እንግሊዘኛቸው፣ በሚማርክ ቅዳሴያቸው፣በበሰሉ ስብከቶቻቸው፣በታጋሽ ፍርዳቸው፣በሰፋ እይታቸውና በወንጌል ፍቅራቸው ወደፊትም አምሳያ እንደማይገኝላቸው ብዙዎች ይስማማሉ፡፡
በቅርቡ 20ኛ ዓመት የሲመት በዓላቸውን ያከበሩ ሲሆን "ፍልሰታ" የተባለ መጽሓፋቸውንም አሳተመዋል፡፡ በቅርቡ በመንበረ ፓትርያርክ ማርያም ቀድሰው ስንብታዊ መልእክታትንም አስተላልፈዋል፡፡
ቅዱስነታቸው የነገረ መለኮት ኮሌጆችንና የካህናት ማሰልጠኛዎችን አስፋፍተዋል፡፡ የቤተክርስቲያናችንን ዓለማቀፋዊ ግንኙነቶች አጠናክረዋል፡፡ ደርግ የወረሳቸውን ቤቶች አስመልሰዋል፡፡ የልማት ተቋማትን አቋቁመዋል፡፡
ከወራት በፊት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ስላረፉ ዓመቱን የቅዱሳን ፓትርያርኮች የዕረፍት ዓመት አሰኝቶታል፡፡ ሽኖዳ ሞት የተርጓሚያን እንጀራ እንደሳሳ ሁሉ በጳውሎስም ሞት የጋዜጠኞች ገበያ ይቀንሳል ተብሎ ተሰግቷል፡፡
ነገ ስለራሱ ይጨነቅ ብለን እንጂ ብዙ ስጋቶች አሉብን፡፡ በፊታችን ተስፋ እሚጣልበት ሰው የለም፡፡ እግዚአብሔር ቤቱን እንዲያስብ እንጸልይ፤የተሸለውን ከእርሱ ብቻ እንጠብቅ!!
ለሚወዱአቸው መጽናናትን ለቤተክርስቲያን ሰላምን ተመኘን፡፡

2 comments:

  1. May Lord have mercy upon the soul of His Holiness Patriarch Abune Paulose of Ethiopia.

    ReplyDelete
  2. የውዳሴው ጎርፍ ሳደርቅ፣ኀዘን ሳያዩ ሄዱ!
    አተኩአቸውም አምናለሁ!
    ግን ማን ያውቃል ጸልዩ!

    ReplyDelete

Tricks and Tips