Friday, August 24, 2012

አሻግሩን



ምልክቱን ካየን በእናንተ እጆች
ካላችሁን ልጆች ልጆች
ልክ እንደ ኖህ ሰብስባችሁ
በመርከቡ አሳርፋችሁ
ምድረበዳ ሳታቆዩን
ንፍር ውሃው ሳይተኩሰን
ዶፍና ጎርፍ ሳያርሰን
እስኪ እንለፍ አሳልፉን
ከንውፅውጽታው አሳርፉን
እንደ ሙሴም ከፊት ምሩን
ቀድሞ ማዳን አስተምሩን
የአበው ልጆች ወዴት ናችሁ
እንዲረዳን ጸሎታችሁ
ውሰዱና በደረቁ
ዛሬም ግብፆች ይደነቁ
የቱ ጋ ናችሁ ሙሴዎቹ
ሲያስጨንቁን ፈርኦኖቹ
አሻግሩና ተሻግራችሁ
እንዲፈጸም ተልዕኮአችሁ

ከደጀ-ሰላም የግጥም መድብል የተወሰደ
(ዘፍቅርተ 2002)

No comments:

Post a Comment

Tricks and Tips