Monday, August 20, 2012

የደም ጠብታ

ጦረ የያዘው ጦረኛ
የመሸበት ፈረሰኛ
አይሁዳውያን እንዳይከሱት
ፈርቶ የመጣው አንድ ዐይና
እርሱ ሎንጊኖስ ጦር ያዘና
ደሙን ቢያፈስ ጎኑን ወግቶ
ማንነቱን ዘንግቶ
ኮለል ያለች የደም ዘለላ
በበቀል ፈንታ ሌላ
ጠብ ያለች የደም ጠብታ
ጠብን ጥልን አጥፍታ
በዐይን ታየች ዐይን አብርታ

 ከደጀ-ሰላም የግጥም መድብል የተወሰደ
(ዘፍቅርተ 2002)

1 comment:

  1. የደሙ ጠብታ የሀጢአትን ተራራ አፍርሶአል!
    የደሙ ጠብታ የሲኦልን ደጆች ሰብሮአል!
    የደሙ ጠብታ የገሀነም ደጆችን አስጨንቆአል!
    ጥሩ ግጥም ነው አትጥፉ

    ReplyDelete

Tricks and Tips