Thursday, August 23, 2012

የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈጸመ


የኦሬንታልና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት፣የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣በሺዎች የሚቆጠሩ አማኞች በተገኙበት የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ ተፈጸመ፡፡ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ካረፉበት ጊዜ ጀምሮ ብዙዎች ሀዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ ትናንት ከ4 ሰዓት ጀምሮ የፍትሀትና የሽኝት መረሀ ግብር ተደርጎላቸዋል፡፡ ሀዘን ሳይሆን በዓል በሚመስል ዝግጅት በክብር ተሸኝተዋል፡፡



ቅዱስነታቸው ለልማት፣ለሰላም፣ለአንድነት፣ለጋራ ጥቅምና ለሃይማኖት እንደሰሩ የኦሬንታልና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት መስክረዋል፡፡ ሕዝቡም አካባቢውን መሞልቶ ሸኝቷቸዋል፡፡ ዕረፍተ ቅዱሳንን ተመኘንላቸው፡፡

No comments:

Post a Comment

Tricks and Tips